በሲያትል ለሚገኙ ቤተ-መዘክር ነጻ መግቢያ ለማግኘት የቤተ-መጽሐፍት ካርድዎን ይጠቀሙ። በአቪዬሽን፣ በተፈጥሮ፣ በሳይንስ እና በኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን ይደሰቱ - ሁሉም በነጻ! ከጉብኝትዎ ቀን ጀምሮ በየ 30 ቀኑ አንድ ጊዜ ወደ ቤተ-መዘክር አንድ ትኬት ማስያዝ ይችላሉ። ከቀኑ 12 ሰዓት በኋላ በየቀኑ አዲስ ትኬቶች ይገኛሉ።
እያንዳንዱ የቤተመፃህፍት ካርድ ባለቤት በየ30 ቀኑ አንድ ትኬት ማስያዝ ይችላል። ቦታው ውስን ነው፣ ስለዚህ በተቻለዎት ፍጥነት ቦታ ይያዙ። ከቀኑ 12 ሰዓት በኋላ በየቀኑ አዲስ ትኬቶች ይገኛሉ።
የሚዝየምና ቀኑን በመጠቀም የመስመር ላይ ማስያዣ ሥርዓቱን ይጠቀሙ። የሚገኝ ትኬት ይጠይቁ።
በቤተ መጻሕፍት ካርድ ቁጥርዎ እና ሚስጥራዊ ቁጥርዎ ይግቡ እና መረጃዎን ያስገቡ።
የታተመ ወይም የኤሌክትሮኒክስ ማለፊያዎትን እና የፎቶ መታወቂያዎን በተመረጠው ቀን ወደ ሚዝየሙ ይዘው ይምጡ። በቤተመጻሕፍት ቦታዎች በነፃ ማተም ይችላሉ።
በቤተ-መዘክር ወይም በቀን ለመፈለግ የመስመር ላይ ቦታ ማስያዣ ስርዓቱን ይጠቀሙ። እያንዳንዱ የቤተ-መዘክር ትኬት ቢያንስ ሁለት የጎልማሳ ትኬቶችን ያካትታል፣ እና አንዳንድ ትኬቶች አራት ወይም ከዚያ በላይ ትኬቶችን ያካትታሉ።
የሚከተሉት ቤተ-መዘክሮች በቤተ-መዘክር ትኬት ፕሮግራም ውስጥ ይሳተፋሉ።
>በነጻ ማለፊያ ፕሮግራማችን ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሚዝየም የታተመ ወይም የኤሌክትሮኒክስ ማለፊያዎን እና የፎቶ መታወቂያዎን ይዘው እንዲመጡ ይጠይቃል። ማለፊያዎ ከቦታ ማስያዣ ማረጋገጫ ኢሜይል የተያያዘው ፒዲኤፍ (PDF) ነው። እባክዎን ትኬት በኢሜይል እንዲላክልዎት ከፈለጉ ኢሜይል ያድርጉልን። በቤተ-መጽሐፍት ውስጥ ያለክፍያ ትኬቶቻችሁን ማተም ትችላላችሁ።
ትኬቶቹ ቦታ ለተያዘለት ሰው ብቻ የሚሠራ ነው። ማለፊያዎን ለመሰረዝ፣ የቦታ ማስያዣ ማረጋገጫ ኢሜይልዎ ላይ ያለውን መሰረዣ ማገናኛ (link) ይጎብኙ። ማለፊያው በተዘረዘረበት ገጽ ላይ፣ "Cancel Booking? (ቦታ ማስያዣውን ይሰርዙ?)" ከሚለው ቀጥሎ "Yes (አዎ)" የሚለውን ይጫኑ።