The Seattle Public Library በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ነፃ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የመማሪያ ፕሮግራሞችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያስፋፋ በደስታ ያበስራል። ይህ ማስፋፊያ ከCarnegie Corporation of New York ለThe Seattle Public Library Foundation በተሰጠ 450,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራ ይሆናል።

እየተሰጠ ያለው ድጋፍ ቤተ መጻሕፍቱ ተጨማሪ የቋንቋ ትምህርት እና የዲጂታል እውቀት ፕሮግራሞችን እንዲያቀርብ ይረዳል ተብሎ ይጠበቃል፣ ከእነዚህም መካከል:

  • የእንግሊዝኛ ንግግር ክበቦች: ለመማር የሚፈልጉ የእንግሊዝኛ ክህሎታቸውን የሚለማመዱበት ምቹ ቦታ ያቀርባል።
  • የእንግሊዝኛ ትምህርቶች: ተሳታፊዎች ለኮሌጅ እንዲዘጋጁ የሚያግዝ የላቀ የእንግሊዘኛ እንደ ሁለተኛ ቋንቋ (English as a Second Language፣ ESL) ትምህርት ያካትታል።
  • የአዋቂዎች የማጠናከሪያ ትምህርቶች: በእንግሊዝኛ፣ በዜግነት እና በመሰረታዊ ክህሎቶች አንድ ለአንድ እና በትንሽ ቡድን ውስጥ የሚሰጡ ትምህርቶችን ያቀርባል።
  • የኮምፒዩተር ትምህርቶች: ተማሪዎች ላፕቶፕ እንዲያገኙ የሚያስችሏቸው በበርካታ ቋንቋዎች የሚሰጡ ትምህርቶች ናቸው።

የሲያትል የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት (The Seattle Public Library፣ SPL) ዋና ቤተ መጻሕፍት ኃላፊ የሆኑት Tom Fay “የCarnegie Corporation በሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ላይ ያለው ኢንቨስትመንት በዚህ ሰአት በጣም አስፈላጊ ነው” ብለዋል። “ለዚህ ለጋስ ድጋፍ ምስጋና ይግባውና የSeattle ስደተኞች እና ጥገኞች ግቦቻቸውን እንዲከታተሉ እና በከተማችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ህይወት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያግዙ ተጨማሪ ፕሮግራሞችን ማቅረብ እንችላለን።” 

የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ ፕሮግራሞች በአሁኑ ጊዜ በThe Seattle Public Library በBeacon Hill፣ Broadview፣ Delridge፣ Lake City፣ NewHolly፣ Northgate እና Rainier Beach ቅርንጫፎች ይቀርባሉ።

ቤተ መጻሕፍቱ በዚህ መኸር መጀመሪያ ላይ በርካታ አዳዲስ ፕሮግራሞችን መስጠት ይጀምራል። በሁለት ዓመቱ የድጋፍ ጊዜ ውስጥ የበለጠ ተጨማሪ ፕሮግራሞችን ይጨምራል።

ፕሮግራሞች በCentral Library እና በInternational District/Chinatown፣ High Point፣ South Park እና Southwest ቅርንጫፎች ውስጥ ይጨመራሉ። የአንዳንድ ፕሮግራሞች አገልግሎት ኦንላይን ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ አንዳንድ በአካል የሚሰጡ ፕሮግራሞች ደግሞ ወላጆች ለመገኘት እንዲመቻቸው ነፃ የሕፃናት እንክብካቤ አገልግሎትን ይሰጣሉ።  ስለእነዚህ ፕሮግራሞች ተጨማሪ መረጃ በዚህ መኸር መጀመሪያ ላይ የሚገኝ ይሆናል።

እነዚህን ፕሮግራሞች ለማቅረብ፣ SPL እንደ Evergreen Goodwill፣ Hopelink፣ Literacy Source፣ Seattle Colleges እና Villa Comunitaria ካሉ ታማኝ የአገር ውስጥ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ይሰራል።

ተጨማሪ መረጃ በቤተ መጻሕፍቱ የአዋቂዎች መማሪያ ገጽ ላይ ያገኛሉ። አንዳንድ ፕሮግራሞች በ www.spl.org/Calendar ላይ ባለው የቀን መቁጠሪያ ላይ ይዘረዘራሉ።

ለThe Seattle Public Library Foundation የተሰጠው ድጋፍ የካርኔጊ "" “Libraries as Pillars of Education and Democracy (ቤተመጽሐፍት የትምህርት እና የዴሞክራሲ ምሰሶዎች)" ተነሳሽነት አካል ሲሆን፣ ይህም በዘጠኝ ግዛቶች ለሚገኙ 11 ቤተመጽሐፍቶች በአጠቃላይ 5 ሚሊዮን ዶላር እየሰጠ ነው። 

ስለ Carnegie Corporation of New York

Carnegie Corporation of New York በጣም አስፈላጊ ናቸው ተብለው በሚታሰቡ ጉዳዮች: ትምህርት፣ ዴሞክራሲ እና ሰላም - በበጎ አድራጎት ድጋፍ አማካኝነት የፖለቲካ ልዩነት ወይም ጽንፍን ለመቀነስ ይሰራል። Carnegie ከትላልቅ የቤተመጽሐፍቶች በጎ አድራጎት ደጋፊዎች አንዱ ነው carnegie.org/libraries