አማርኛ

አማርኛ : ልጆችዎን እናስተናግዳለን?

Amharic Section

ልጆችዎን እናስተናግዳለን?

(We welcome children!)

 

ልጅዎ ማንበብ እንዲማሩና በትምህርት ቤት እንዲሳካላቸው ለመርዳት ይፈልጋሉ? በሁሉም የቤተ መጻፍት ቅርንጫፎች ልጆችን እናስተናግዳለን። በመኖርያ ሰፈርዎ በሚገኘው ቅርንጫፍ የልጆች ቦታን ይጎብኙ። እንዲሁም ለሁሉም የእድሜ ደረጃ የሚሆኑ መጽሃፎችን፤ ድቪዲዎችንና ሙዚቃ በአማርኛና በእንግሊዚኛ ይመልከቱ። ልጆችዎ የግላቸውን የቤተ መጻህፍት ካርዶች ሊያገኙም ይችላሉ። ደግሞም በብዙ ቋንቋዎች የልጆች ፕሮግራሞች አሉን። በታርክ ትረካ ወይም (Play and Learn Group) የጫዋታና ትምህርት ቡድን ሰዓት ከልጆችዎ ጋር ይካፈሉ።

 

በቤተ መጻፍትዎ ኮረዳና ጎረምሳ ልጅ መሆን ታላቅ ነገር ነው! በአብዛኞቹ የቤተ መጻፍት ቅርንጫፎች ለኮረዳና ጎረምሳ ልጆች የተከለከለ ቦታዎች አሉን፤ ለኮረዳና ጎረምሳ ልጆች የሚሆኑ መጽሃፎችና መጽሄቶች እንዲሁም ለተማሪዎች መሰብሰቢያ ቦታዎች ያሉት። በግጥም መግጥምያና በጨዋታ ዉድድር ምሽታችን ላይ ይገኙ! በኮረዳና ጎረምሳ ልጆች መጽሃፍ ቡድን፤ ስንጠረዥ(ቼዝ) ክበብ ይካፈሉ ወይም የዘፈን ግጥም ወይም የቀልድ መጽሃፎችን ለመጻፍ የስራ ጥናት ይካፈሉ። በተጨማሪም ኮረዳና ጎረምሳ ልጆች ጽሁፍ መጻፍ እንዲማሩ፤ ለኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎች እንዲዘጋጁና ለኮሌጅ የሚከፍሉትን ገንዘብ እንዲያገኙ የሚረዱ ትምህርቶችን እናቀርባለን።

 

ኮረዳ ወይም ጎረምሳ ልጅዎ በትምህርት ቤት እርዳታ ያስፈልጋታል ወይም ያስፈልገዋል? ቤተ መጻፍቱ “Homework Help” (የቤት ስራ መርጃ) ማእከሎች በብዙ ቅርንጫፎች አሉት። “Homework Help” መጻሃፍት ቤቱ የሚያቀርባቸው ፈቃደኞች ለህጻናት፤ ለኮረዳና ጎረምሳ ልጆች በብዙ የትምህርት ዓይነቶች በታርክ፤ እንግሊዚኛ፤ ጽሁፍ፤ ሳይንስና፤ ሂሳብ ላይ እርዳታ ሊያደርጉ ይችላሉ። በተለይ ለአዲስ እንግሊዚኛ ተናጋሪዎች እርዳታ ለማቅረብ ጥሩ ናቸው። "Homework Help" በተጨማሪ የቤት ስራ እርዳታ በኦንላይን በእንግሊዚኛ በ www.spl.org. ይቀርባል።

የቤተ፡መፃፍቱ፡ቦታዎች፡ካርታ።
ለነፃ፡የቤተ፡መፃፍቱ፡ካርዶ፡ይመዝገቡ።