አማርኛ

አማርኛ : SPL Hotspot

Russian Section

SPL Hotspot

SPL HotSpot - Connecting Seattle

መጻፍትዎ የ SPL HotSpot ይዋሱ።

የ SPL HotSpot ለመጠቀም ቀላል ሲሆን፣ ታብሌት፣ ላፕቶፕ እና ሌሎች በ Wi-Fi–መሥራት የሚችሉ መሣሪያዎችን ከኢንተርኔት የሚያገናኝ ተንቀሳቃሽ መገናኛ HotSpot ነው።

በ 4G LTE እና 3G የኢንተርኔት መሥመሮች እስከ 15 ያህል መሣሪያዎች ማገናኘት ይችላሉ፣ እንዲሁም ሌሎች ከውጭ የሚገጠሙ መሣሪያዎች ባትሪን መሙላት ይችላሉ።

ማወቅ የሚያስፈልገኝ ምንድን ነው?

 • መሣሪያውን መዋስ የምችለው እንዴት ነው?
  ወደ ቤተ መጻፍት ቅርንጫፍዎ ብቅ ይበሉ ወይም ተቀማጭ እንዲሆንልዎት የቤተ መጻፍት ካርድዎን ይጠቀሙ እና እንደ ማንኛውም ዓይነት እቃ ይዋሱ። (ደግሞም ያስታውሱ የዋየርለስ ኢንተርኔት  ምንም ወጪ ሳያስወጣዎት በማንኛውም በ Wi-Fi–ሊሥራ በሚችል ላፕቶፕና የዋየርለስ መሣሪያ በሁሉም የቤተ መጻፍት ቦታዎች ማግኘት ይቻላል።)
 • እነዚህን መሣሪያዎች መዋስ የሚችል ማነው?
  ተቀባይነት ያለው የቤተ መጻፍት ካርድ ያለው ማንኛውም ሰው የ SPL HotSpot መዋስ ይችላል። የቤተ መጻፍት ካርድ የለዎትም? >እዚህ ማመልከቻ ያስገቡ.
 • ለምን ያህል ጊዜ ላቆየው እችላለሁ?
  ለ 21 ቀናት መዋስ ይችላሉ። ቀኑ ያለፈባቸው HotSpot ቀናቸው ካለፈ ከ 24 ሰዓት በኋላ የኢንተርኔት መሥመራቸው እንዲቋረጥ ይደረጋል።
 • የምመልሰው እንዴት ነው?
  የ SPL HotSpot ን እንደ ሌሎች እቃዎች ሁሉ በማንኛውም የቤተ መጻፍት አድራሻ ወይም መጻፍ መመለሻ ቦታ ሊመልሱ ይችላሉ። መሣሪያውን ከዋናው ማሸጊያና መገጣጠቢያዎች፣ ከሁሉም ጋር መመለስ አለብዎት። እባክዎን መሣሪያውን ከመመለስዎ በፊት ባትሪውን በደንብ ይሙሉት።
 • የማሳድሰው እንዴት ነው?
  መሣሪያውን ለማደስ በ የኢንተርኔት መዝገብዎ (አካውንት) ውስጥ በመግባት ወይም በማንኛውም የቤተ መጻፍት ቦታ ፣ እንደማንኛውም እቃ ሁሉ ማሳደስ ይችላሉ።
  ፣ እንደማንኛውም እቃ ሁሉ ማሳደስ ይችላሉ።
 • ምን ያህል ወጪ ያስወጣል? !--Borrowing and using the device is free! If the device is lost or damaged beyond repair, a $199 fee will be charged to your Library account.--> መሣሪያውን ተውሶ ለመጠቀም በነጻ ነው! መሣሪያው ከጠፋ ወይም ሊጠገን የማይችል ሆኖ ከተበላሸ፣ $199 ክፍያ በቤተ መጻፍት ሂሳብዎ ላይ እንዲከፍሉ ይሆናል።
 • ሌሎች ጥያቄዎች?
  የቤተ መጻፍት ሠራተኛን ይጠይቁ

 

ባልደረባ ድርጅቶች

ለ SPL HotSpot ፕሮግራም ድጋፍ የተደረገው በ

Google  The Seattle Public Library Foundation

 

ስለዚህ ፕሮግራም ተጨማሪ መረጃ

Get the User Guide
Ask a Librarian
ለነፃ፡የቤተ፡መፃፍቱ፡ካርዶ፡ይመዝገቡ።