አማርኛ

አማርኛ : እንኳን ደህና መጣህ

Amharic Section

ዋና ዳይሬክተር እና ዋና የቤተመጽሐፍት ባለሙሉ መልዕክት

በጊዜ ሂደት፣ የህዝብ (መንግስት) ተቋማት ማን እንደሆኑና ምን እንደሚያምኑ ማረጋገጥ የሚያግዝ ነው። የሲያትል የህዝብ ቤተ መፃህፍት የእንኳን ደህና መጡ ቦታ ለእርስዎ ማዘጋጀቱን እንደሚቀጥል ማወቁ ጠቃሚ ነው።

ቤተ መፃህፍት ተቋማትን በሙሉ ሁልጊዜም ይቀበላሉ። መኖራችንም ይህንን መሰረት ያደረገ ነው። ስለ ሲያትል የህዝብ ቤተ መፃህፍት፣ እሴት የሚናገር አንድ የመሰረተ ሀሳብ መመሪያ አለ፡-

አጠቃላይ ማህበረሰቡን ማክበርና መያዝ።

ሁሉንም መቀበላችንን ለማረጋገጥ ሁሉም ሰው ወደ ቤተ መፃህፍቱ ቢመጣ ተቀባይ እንደሚሆን እንዲሰማው የሲያትል ልዩ ልዩ ሀሳቦችን ለማስተናገድ ጥረት እናደርጋለን። ከዘር፣ ከብሄር፣ ከሀይማኖት፣ ከባህል፣ ከጾታዊ አመለካከት፣ ከእምነት፣ ከገቢ ወይም ከአካል ጉዳት አንጻር ቤተ መፃህፍቱ ፍላጎቶችንና የሚጠበቅበትን እያንዳንዱን ነገር ለማሟላት ይተጋል። የሲያትል የህዝብ ቤተ መፃህፍት በእውቀት ላይ ያልተመሰረተ ሀሳብ፣ ማጣጣልና መገለልን በንቃት ለመዋጋት ድጋፍ ያደርጋል።

በራችን ሁልጊዜም ክፍት ነው፣ ሁልጊዜም ወደ ቤተ መፃህፍቱ መምጣት እንደሚችሉ እናስባለን። እንዲሁም ለህይወትዎ የሚረዱ ብዙ የእውቀት ምንጮች አሉ።

እርስዎና ማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ሰው በሙሉ የዘወትር ተጠቃሚ ሆኑም አልሆኑ፣ ተማሪ፣ ጎብኝ፣ በእድሜ የገፉ፣ ስራ ፈላጊዎች፣ ስደተኞች ወይም የቤት ችግር ያለባቸው፤የእውቀት ምንጮቻችንንና ባለሙያ ድጋፎችን ማግኘት መቻላቸውን ለማረጋገጥ 27 ቤተ መፃህፍት በተለያዩ አይነት አካባቢዎች እንዲከፈቱ ማድረጋችንን ስንገልጽ በኩራት ነው።

አለም በየጊዜው የሚለዋወጥ ቢሆንም፣ እዚህ ግን አንድ የማይቀየር ነገር አለ - የሲያትል የህዝብ ቤተ መፃህፍት በር ሁልጊዜም ክፍት ነው - ቪዛ፣ አባልነት ወይም መታወቂያ አያስፈልግም።

ጥያቄ የለም፣ ጥርጣሬ የለም። ቤተ መፃህፍታችን ለሁሉም ክፍት ነው።

ምንም አያስፈልግም። ምንም የሚረጋገጥ ነገር የለም። እንኳን ደህና መጡ።

chief librarian signature

Marcellus Turner፣ ዋና ዳይሬክተር እና ዋና የቤተ መፃህፍት ባለሙያ ናቸው

Marcellus Turner, Executive Director and Chief Librarian

Contact Your Chief Librarian


206-386-4147
chieflibrarian@spl.org


1000 Fourth Ave.
Seattle, WA
98104-1109