አማርኛ

አማርኛ : ለእንግሊዚኛ፤ ለትምህርት ቤት ወይም ዜጋ ለመሆን እርዳታ ያስፈልግዎታል?

Amharic Section

ለእንግሊዚኛ፤ ለትምህርት ቤት ወይም ዜጋ ለመሆን እርዳታ ያስፈልግዎታል?

(Need help with English, school or becoming a citizen?)

 

እንግሊዚኛ እየተማሩ ነው? እንዲረዱዎት ብዙ መጽሃፎች፤ ሲዲዎችና ሌሎችም አሉን። በራስዎ የመማር ፍጥነት ችሎታ መሰረት እንግሊዚኛ ለመማር ኮምፒተሮቻችንን ይጠቀሙ። ደግሞም ቤተ መጻፍቱ ESL ትምህርቶችን በብዙ ቅርንጫፎች ይሰጣል። ወይም በ "Talk Time" (የንግግር ጊዜ) የዉይይት ቡድን ይካፈሉ፤ የእንግሊዚኛ ቋንቋ ችሎታዎን ከሌሎች የእንግሊዚኛ ቋንቋ ተማሪዎች ጋር ይለማመዱ እንዲሁም በማህበረሰብዎ ውስጥ እንግሊዚኛ ስለሚማሩባቸው መንገዶች ይወቁ።

 

ለ GED ወይም የዩኤስ ዜግነት ፈተና ለመዘጋጀት እርዳታ ያስፈልግዎታል? ስለ ኢሚግሬሽን፤ ጤና ጥበቃ ወይም ስራ ፍለጋ መረጃዎች ያስፈልጉዎታል? ልንረዳ እንችላለን! የዜግነት ትምህርቶችን በማእከላዊው ቤተ መጻህፍት መማር ይችላሉ። ዜጋ እንዴት መሆን እንደሚቻል የሚገልጹ የአማሪኛ መጽሄቶች አሉን። ደግሞም ደብዳቤ ለመጻፍና የስራ ልምዶችን ለመጻፍ የሚረዱዎት ፕሮግራሞች አሉን። ይመልከቱ…በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የእለት ከእለት ኑሮን ለመልመድ የሚርዱዎት ብዙ መጽሃፎች ወይም እቃዎች አሉን።

የቤተ፡መፃፍቱ፡ቦታዎች፡ካርታ።
ለነፃ፡የቤተ፡መፃፍቱ፡ካርዶ፡ይመዝገቡ።