አማርኛ

አማርኛ : የምጀምረው እንደት ነው?

Amharic Section

የምጀምረው እንደት ነው?

(How do I get started?)

 

መጥጠዉ የቤተ መጻፍት ካርድ ይዉሰዱ! ቀላል እንዲሆን እናደርጋለን!የቤተ መጻፍት ማመልከቻ ይሙሉና ነጻ የቤተ መጻፍት ካርድዎን ይዉሰዱ። በአብዛኛው ኪንግ ካዉንቲ አካባቢ የሚኖሩ፡ የሚሰሩ ወይም ትምህርት ቤት የሚማሩ ከሆኑ፡ ለነጻ ካርድ ብቁ ነዎት።

 

ቤተ መጻፍቱ ምን እንዳለው እርግጠኛ አይደሉም? ወደ ቤተ መጻፍቱ ሲመጡ፡ ምልክቶቻችን ወደት መሄድ እንደሚስፈልጉ ይመሩዎታል። የስራ ባልደረቦቻችን እርዳታ ለማቅረብ ደስተኞች ናቸው። እንዲሁም የኦንላይን የቤተ መጻፍት ዝርዝር(ካታሎግ) ይመልከቱ። ዝርዝሩ የሚገኘውን ማንኛዉም መጽሃፎች ወይም ዕቃ ይዘረዝራል። በግምት ከ2000000 በላይ የሚሆን መጽሃፎች ወይም ዕቃዎች ስብስብ አለን!

 

ከቤትዎ ሆነው የመጽሃፍ ተራ ለመያዝ ይፈልጋሉ? የሚፈልጉት መጽሃፍ ሌላ ሰው ተዉሶት ከሆነ፤ በኦንላይን ወይም ለሰፈርዎ ቅርንጫፍ ቤተ መጻፍት ወይም Borrower Services Department (የተዋሽዎች አገልገሎት ክፍል) 206-386-4190 በመደወል ተራ መያዝ ይችላሉ። የበተ መጻፍት ካርድዎ ቁጥር ያስፈልግዎታል። አብዛኞቹን መጽሃፎች ወይም ዕቃዎች በጣም በሚያመችዎት ቅርንጫፍ ሄደው መውሰድ እንዲችሉ ወደ ቅርንጫፉ ቤተ መጻፍት ሊላኩ ይችላሉ።

 

የሚፈልጓቸውን መጽሃፍት ወይም ዕቃዎች ካገኙ አስመዝግበው መዋስ ነው። እርዳታ ወደሚያደርጉሎት የቤተ መጻፍቱ ሰራተኘች መጽሃፎቹን ወይም ዕቃዎቹን መውሰድ ይችላሉ። ወይም ካሉን “self-check out” (በራስ አገዝ መዋሻ) ጣቢያዎች ውስጥ አንዱን ይጠቀሙ።

 

መጽሃፎቹን ወይም ዕቃዎቹን መመለሻው ጊዜ ሲደርስ በቤተ መጻፍት ቅርንጫፎች ከሚገኙት “bookdrops” (መጽሀፍ ማጠራቀሚያዎች) ውስጥ አንዱን መጠቀም ይችላሉ። አብዛኛዎቹ በቀን ለ24 ሰዓታት ክፍት ናቸው።

 

በቤተ መጻፍቱ የሚደረግ ምን ነገር አለ?

 

(What is there to do at the Library?)

 

በቤተ መጻፍቱ ኮምፒተር መጠቀም ይፈልጋሉ? ኢሜይል ለማየት ወይም በየቀኑ በማንኛውም የቤተ መጻፍት ቅርንጫፍ ካርድዎና PIN (የግል መታወቂያ ቁጥር) በማስገባት ለዘጠና ደቂቃ ኢንተርነት ለመጠቀም ይችላሉ። ሁሉም የቤተ መጻፍት ቅርንጫፎቻች የአየር ላይ መገናኛ(ዋየርለስ) ስላላቸው ላፕቶፕን በማምጣት ይጠቀሙባቸው።

 

ኮምፒተርን እንዴት ስለመጠቀም ትምህርት መማር ይፈልጋሉ? የተወሰነ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ላላቸው ሰዎች የሚሰጠውን የኮምፒተር ትምህርት ለመማር ይመዝገቡ።

 

መጽሃፍ ማንበብ ይወዳሉ? የቤተ መጻፍቱ ኦንላይን ዝርዝር(ካታሎግ) መጽሃፎችን፤ ሙቪዎችንና ሙዚቃን ባአማርኛ ለመፈለግ ይጠቀሙበት። ወይም ይጠይቁን… ለመላው ቤተሰብዎ መጽሃፎችን ወይም ዕቃዎችን ማግኘት እንዲችሉ እንረዳዎታለን!

 

ከሃገር ቤት ግኑኝነት ለማድረግ ይፈልጋሉ ወይም ልጆችዎ ባህላዊ ልማዳቸዉንና የሃገር ቤት ቋንቋቸዉን እንዲያጠኑ መርዳት ይፈልጋሉ? ዓለም አቀፍ በኦንላይን ጋዘጣዎችን ያንብቡ፤ ስለሃገር ቤትዎ ሙዚቃን፡ ፍልሞችን ወይም መጽሃፎችን ይዋሱ።

የቤተ፡መፃፍቱ፡ቦታዎች፡ካርታ።
ለነፃ፡የቤተ፡መፃፍቱ፡ካርዶ፡ይመዝገቡ።