(How do I get started?)
መጥጠዉ የቤተ መጻፍት ካርድ ይዉሰዱ! ቀላል እንዲሆን እናደርጋለን!የቤተ መጻፍት ማመልከቻ ይሙሉና ነጻ የቤተ መጻፍት ካርድዎን ይዉሰዱ። በአብዛኛው ኪንግ ካዉንቲ አካባቢ የሚኖሩ፡ የሚሰሩ ወይም ትምህርት ቤት የሚማሩ ከሆኑ፡ ለነጻ ካርድ ብቁ ነዎት።
ቤተ መጻፍቱ ምን እንዳለው እርግጠኛ አይደሉም? ወደ ቤተ መጻፍቱ ሲመጡ፡ ምልክቶቻችን ወደት መሄድ እንደሚስፈልጉ ይመሩዎታል። የስራ ባልደረቦቻችን እርዳታ ለማቅረብ ደስተኞች ናቸው። እንዲሁም የኦንላይን የቤተ መጻፍት ዝርዝር(ካታሎግ) ይመልከቱ። ዝርዝሩ የሚገኘውን ማንኛዉም መጽሃፎች ወይም ዕቃ ይዘረዝራል። በግምት ከ2000000 በላይ የሚሆን መጽሃፎች ወይም ዕቃዎች ስብስብ አለን!
ከቤትዎ ሆነው የመጽሃፍ ተራ ለመያዝ ይፈልጋሉ? የሚፈልጉት መጽሃፍ ሌላ ሰው ተዉሶት ከሆነ፤ በኦንላይን ወይም ለሰፈርዎ ቅርንጫፍ ቤተ መጻፍት ወይም Borrower Services Department (የተዋሽዎች አገልገሎት ክፍል) 206-386-4190 በመደወል ተራ መያዝ ይችላሉ። የበተ መጻፍት ካርድዎ ቁጥር ያስፈልግዎታል። አብዛኞቹን መጽሃፎች ወይም ዕቃዎች በጣም በሚያመችዎት ቅርንጫፍ ሄደው መውሰድ እንዲችሉ ወደ ቅርንጫፉ ቤተ መጻፍት ሊላኩ ይችላሉ።
የሚፈልጓቸውን መጽሃፍት ወይም ዕቃዎች ካገኙ አስመዝግበው መዋስ ነው። እርዳታ ወደሚያደርጉሎት የቤተ መጻፍቱ ሰራተኘች መጽሃፎቹን ወይም ዕቃዎቹን መውሰድ ይችላሉ። ወይም ካሉን “self-check out” (በራስ አገዝ መዋሻ) ጣቢያዎች ውስጥ አንዱን ይጠቀሙ።
መጽሃፎቹን ወይም ዕቃዎቹን መመለሻው ጊዜ ሲደርስ በቤተ መጻፍት ቅርንጫፎች ከሚገኙት “bookdrops” (መጽሀፍ ማጠራቀሚያዎች) ውስጥ አንዱን መጠቀም ይችላሉ። አብዛኛዎቹ በቀን ለ24 ሰዓታት ክፍት ናቸው።